22 February, 2012
አንድ ካናዳዊ በኢትዮጵያ የንጹህ ውህ ፕሮጀክትን ለመርዳት የ 12,000 ኪሜ የቢስኪሌት ጉዞ ጀመሩ
በኢትዮጵያ ለሚካሄድ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ገንዘብ ለማሰባሰብ የ 12,000 ኪሎሜትር የቢስክሌት ጉዞ የጀመሩት ካናዳዊ በጎ አድራጊ ማይክል ፖል እስካሁን ባለው ጊዜ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ማሰባሰባቸውን አስታውቀዋል።
በካናዳ ኤድመንተን የሚኖሩት የ55 አመት እድሜ የሆኑት በጎ አድራጊ ከካይሮ እስከ ኬፕታውን በብስኪሌት በመጓዝ ነው በቦንኬ ኢትዮጵያ ላሉት ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ወሀ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት የወሰኑት። እስካሁን ባለው ጊዜ ከግብጽ ወደ ሱዳን ከሱዳን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘዋል።
- Listen: የመጠጥ ውሀ ውጥን ለመርዳትን ያድምጡ
MP3
VOA 60 - Africa
To view our site properly you may need to install the Geez font : Download Now
If you are still having problems viewing our site you may need to change your browser settings. FAQ: Update Browser Settings