06 September, 2010
የብሪታንያ የአለም አቀፍ ልማት ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ምርጫ ማጠቃለያ ሪፖርት
የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ቡድን በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ
ለሚያወጣው ማጠቃለያ ሪፖርት መንግስት በቅንነት ምላሽ እንደሚሰጥ
የብሪታንያ የአለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ተስፋቸውን ገለጹ
“ከ18 ወራት በፊት እዚህ በነበርኩበት ወቅት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ህግ መለወጡ በጣ ካሳሰባቸው ወገኖች ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ተነጋግሬያለሁ። አሁን የተረዳሁት ነገር ምንድነው በዚያን ጊዜ ከተገለጹት
ስጋቶች የተወሰኑት በተግባር አልታዩም። ሆኖም የምናተኩርበት ጉዳይ
ይሆናል።”
የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ቡድን በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ የሚያወጣው ማጠቃለያ ሪፖርት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የብሪታንያ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ ይህ ማጠቃለያ ሪፖርት ይፋ በሚወጣበት ጊዜ ከኢትዮጵያ ተስፋ የሚያደርጉት መኖሩን ተናግረዋል።
አንድሪው ሚሸል በአለም በትልቅነቱ ሁለተኛው የሆነውን አገራቸው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የልማት ዕርዳታ ኢትዮጲያውያንን በምን አይነት ሁኔታ እየጠቀሙበት መሆኑን መመልከት የጉብኝታቸው አንዱ ዓላማ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ለዝርዝሩ ከአዲስ አበባ የተጠናቀረውን ዘገባ ያድምጡ።
VOA 60 - Africa
To view our site properly you may need to install the Geez font : Download Now
If you are still having problems viewing our site you may need to change your browser settings. FAQ: Update Browser Settings