01 September, 2010
የኢትዮጵያ ብር የውጭ ምንዛሪ አቅም ተቀነሰ
የኢትዮጵያን የምጣኔ ኃብት ዕድገት ለማሳደግ የተያዘው ጥረት አካል መሆኑ የተነገረለትን ዕርምጃ የምጣኔ ሃብት ባለ ሞያዎች በአዎንታ የተቀበሉት ቢሆንም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል የሚል ሥጋት አሳድሯል
ፎቶ፡ VOA
6ዶላር ከ06 ሳንቲም=100ብር
«የሚንገታገተውን የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት፤» ርምጃውን በአዎንታ የተቀበሉት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF የአዲስ አበባ ተጠሪ፥ Sukhwider Singh Toor «አሁን ባለው ደረጃ ከውጭ የሚገዙት ሸቀጦች እጅግ አስፈላጊ በመሆናቸው መጠናቸውን መቀነስ ስለማይቻል የውጭ ንግዱ ዘርፍ ያን ያህል ለውጥ ሊያመጣ አይችልም።
ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገችው እርምጃ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ቀድሞ ከነበረው የ17 በመቶ ብልጫ ይኖረዋል።
የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት IMF የአዲስ አበባ ተጠሪ፥ Sukhwider Singh Toor ጨምሮ አንዳንድ የምጣኔ ሃብት ባለ ሞያዎች በአዎንታ የተቀበሉት ቢሆንም፤ ተገቢ በሆነ የገንዘብ ፖሊሲ እንዲደገፍ የሚሹ መሆናቸውን ይናገራሉ።
ኢትዮጵያው ላለፉት ሰባት ዓመታት በተከታታይ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማስመዝገቧን የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቆይቷል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና በተባበሩት መንግስታት በቅርቡ ይፋ የተደረገ የአገራትን የድህነት ይዞታ የሚያሳይ የጥናት ሠነድ በበኩሉ ኢትዮጵያን ከኒጀር ቀጥሎ የዓለም ሁለተኛዋ ደሃ አገር ማድረጉ ይታወሳል። የውጭ ምንዛሪ ቅናሹን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጠናቀረውን ዘገባ ዝርዝር ያድምጡ።
- Listen: የኢትዮጵያ ብር የውጭ ምንዛሪ ቅነሳ የተመለከተ ዘገባ ያዳምጡ
MP3
VOA 60 - Africa
To view our site properly you may need to install the Geez font : Download Now
If you are still having problems viewing our site you may need to change your browser settings. FAQ: Update Browser Settings