08 September, 2010
የባቱ ባልቻ አባነፍሶ ት/ቤትና የአሜሪካ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጉብኝት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የልጆች ጉዳይ አማካሪ ሱዛን ጃኮብስ
እስካሁን ባዩት የት/ቤቱ ስራ መርካታቸውን ገለጹ
“አሜሪካውያንም የሀገራቸው ህጻናት ወደ ውጭ ሀገራት በጉዱፈቻ እንዲሄዱ
ይፈቅዳሉ። ባለፈው አመት ከአገር ውጪ በጉዲፈቻ የሄዱት አሜሪካውያን
ህጻናት ቁጥር ወደ 50 ገደማ ነው። አሜሪካውያን በየአመቱ 120,000 ህጻናትን
በጉዲፈቻ የምንወስድ መሆናችን ኢትዮጵያውያንን ሊያስገርም ይችላል። ከነዚህ
ውስጥ ደግሞ 100 ሺዎቹ ከራስዋ ከአሜሪካ ናቸው።”
ከ2 አመት በፊት የተቋቋመው የባቱ ባልቻ አባነፍሶ ት/ቤት አቅም የሌላቸውን ወላጆች ለመርዳት ታስቦ ነው፡፡ ተመስገን ደምሰው በዚህ ት/ቤት ለመማር እድሉን ካገኙት ህጻናት አንዱ ነው፡፡ ወደፊትም ሐኪም መሆንን ይመኛል፡፡
ለማስተማር እና ለማሳደግ አቅም ከሌላቸው ቤተሰቦች ውስጥ አንዷ ሮዛ መሀመድ ሲሆኑ ይህንን ዕድል ልጃቸው ባታገኝ ኖሮ እጣ ፋንታዋ ከባድ ይሆን እንደነበር ጠቅሳለች፡፡
የአሜሪካ ከፍተኛ የልኳን ቡድን ጉብኝቱ አላማም፤ ታዳጊዎች ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ መመልከት ነበር፡፡
VOA 60 - Africa
To view our site properly you may need to install the Geez font : Download Now
If you are still having problems viewing our site you may need to change your browser settings. FAQ: Update Browser Settings