06 September, 2010
ቃለ ምልልስ ከባህልና ማኅበረሰብ እንግዳ፥ ገጣሚ ዓለማየሁ ታዬ ጋር።
ልክ እንደኛው ቅኔ የእኛን ቅኔ በሁለት መንገድ እንደምትተረጉመው ሁሉ፤ ሃይኩንም አንብበህ በሁለት መንገዶች ነው የምትተረጉመው። የቡድሂዝምን ፍልስፍናና አስተምህሮ አውቀህ ሃይኩን ስታነብና ሳታውቅ ስታነብ የተለያየ ትርጉም ነው የሚሰጥህ።
«”በበጋ የረጋው ወንዝ፤
የሚንሳፈፍ ቅጠል ላይ ጣይ የምትሞቅ፤
ሙጫ እንቁራሪት፤”...ቀለል ያለች የተፈጥሮን ትዕይንት የምታሳይ ተራ ሃይኩ ናት። ይሁን እንጂ የቡድሂዝም ፍልስፍናን ለሚያውቅ ሰው፤ ከዚህ ቀደም ምን ያህል በሙላትና በኃይል ይፈስ የነበረው ወንዝ ሲረጋ፥ የነገሮችን ጊዜያዊነት የነገሮችን ማለፍ፤ ”የሚንሳፈፍ ቅጠል ላይ ጣይ የምትሞቅ ሙጫ እንቁራሪት፤” የሚለው ደግሞ ተፈጥሮ በስቃይ ዑደት ውስጥ መመላለሷን ያሳየዋል።»
«የዓለማየሁ ሩባያት፤» «ሃይኩ፤» እና «ግራፊቲ፤» በሚል ርዕስ ለህትመት በበቁ ሶስት የግጥም መፃህፎቹ መነሻነት ለእንግድነት ከጋበዝነው ወጣቱ ገጣሚ ዓለማየሁ ታዬ ጋር የጀመርነው ውይይት ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ቃለ ምልልስ በሃይኩና ግራፊቲ ላይ ያተኩራል።
የአስራ ስድስተኛውን ክፍለ ዘመን ጃፓናዊ ባለ ቅኔ ባሾን፥ ባለ ሦሥት መስመሯን ሃይኩንና የቡድሃ ዕምነት ፍልስፍናን ምን ያገናኛቸው ይሆን?
ዓለማየሁ «እንዴታ!» ይላል።
ባህልና ማኅበረሰብን ያድምጡ።
- Listen: ባህልና ማኅበረሰብን ያድምጡ
MP3
VOA 60 - Africa
To view our site properly you may need to install the Geez font : Download Now
If you are still having problems viewing our site you may need to change your browser settings. FAQ: Update Browser Settings