blank

Inside VOA | Contact VOA News

ልዩ ዘገባዎች - አሜሪካ

USA Votes 2010

ማክሰኞ ጥቅምት 23, በ50ውም የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች መራጮች ግዛቶቹን የሚያስተዳድሩ ገዢዎች ይመርጣሉ። የአካባቢ ጉዳዮቻቸውን በብሄራዊው ምክር ቤት መድረክ ትኩረት እንዲያገኝ ለሚያደርጉላቸው ፖለቲከኞችም ድምፃቸውን ይሰጣሉ።

የአገሪቱ ልብ ትርታ በነገው የብሄራዊ ሸንጎ ሸንጎ፥ «የትኛው አሸናፊ ይሆናል?» የሚለውን የተከተለ ነው። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ምርጫ የሚመለከታቸው መላው የህግ አውጭው ምክር ቤት አባላትና በየ6 ዓመቱ ከሚመረጡት የህግ መወሰኛው ምክር አባላት አንድ ሦሥተኛው በቀጣዩ ምክር ቤቶች የሚኖራቸው ሚና ማክሰኞ ይወሰናል። ውጤቱም የግለሰብ ዕጩዎቹን ብቻ ሳይሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት፥ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2008 በተካሄደው ከፍተኛ ድምፅ በተመረጡት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራቲክ ፓርቲና በተቀናቃኙ የሪፐሊካን ፓርቲ መካከል የቀጣዩን የፕሬዝዳንቱን አጀንዳዎች ስኬት ጭምር ይወስናል።

USA Votes 2010 USA Votes 2010

በዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤትና የአገረ ገዢዎች ምርጫ ነገ ማክሰኞ ይካሄዳል።

ለተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች በጠቅላላ ፥ ከመወሰኛው ደግሞ ለአንድ ሦስተኛው፣ እንዲሁም ብዙ ትኩረት ለሣቡ የአገረ ገዥዎችም ምርጫዎች ህዝቡ ድምፁን ይሰጣል።

የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤቶች ምርጫና ዓለም አቀፍ አንድምታው

ሪፐብሊካኖች ምርጫውን አሸንፈው ሁለቱንም ምክር ቤቶች ወይም አንዱን ብቻ እንኳን ከቆጣጠሩ፥ የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች አስመልክቶ በርከት ያሉ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ።

የተወካዮች ምርጫ በዩናይትድ ስቴትስ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ማክሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. እንደራሴዎቹን ይመርጣል፡፡

ሚድ-ተርም ምርጫ ምንድነው?

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትን ለመቆጣጠር በዕጩ እንደራሴዎች መካከል የሚካሄደው የምረጡኝ ዘመቻ ተጠናክሮ ሰንብቷል።

USA Votes 2010

በዚህ አጋማሽ የምርጫ ዘመን ወቅት፣ የአሜሪካ ድምፅ ሰጪዎችን ስለገጠሟቸው ስለነዚህ ጠቃሚ ጉዳዮች፣ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የአፍሪቃ ክፍል፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአድማጮቻችንን አስተያየት ሊሰማ ይወዳል።

Poll

በዚህ ምርጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስን የገጠማት ከፍተኛው ጉዳይ ምንድነው?

ውጤቱን ይመልከቱ »

September 11: Ten Years After

Poll

የአጋማሽ ጊዜ ምርጫው በኦባማ አስተዳደር ላይ ምን አንደምታ/ተጽዕኖ ይኖረዋል?

ውጤቱን ይመልከቱ »