በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕገ መንግሥቱ ለሀገራዊ ምክክር እንዲቀርብ ተጠየቀ


ሕገ መንግሥቱ ለሀገራዊ ምክክር እንዲቀርብ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ ሕገ መንግሥቱ እና የፌደራል ሥርዓቱ አወቃቀር የተካተቱበትና በዐሥራ አንድ ነጥቦች ያደራጃቸው አጀንዳዎች ለምክክር እንዲቀርቡ መጠየቁን አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አደራጅቶ ካስረከባቸው አጀንዳዎች መካከል፣ የአገሪቱን የፖለቲካ ባህል፣ የዘላቂ ሰላም ግንባታን፣ የመሬት አጠቃቀምን፣ የሀብት እና የሥልጣን ክፍፍልን የሚመለከቱ ጉዳዮች እንደሚገኙባቸው፣ የምክር ቤቱ አማካሪ ዶር. ሞገስ ደምሴ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ለኹሉ አቀፍ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እየቀረቡ ያሉ አጀንዳዎችን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ በበኩላቸው፡- የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አጀንዳ፣ በአብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚነሣ ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG